ዋልታ ረገጥ ጠስሜት መለዋወጥ:-የሁለት ጽንፎችና የባለራእዮች ህመም
- Naomie Deborah Tilahun

- Jun 21
- 2 min read
በ ናሄሜ ዲቦራ ጥላሁን
አብዛኛውን ግዜ እንደ አንድ ከአይምሮ መታወክ ሁኔታ ጋር እንደሚኖር ሰው ሆኜ ስመለከተው ብዙ ሰዎች ሚዛንን መጠበቅ ብለው የሚጠሩትን ሀሳብ ለማግኘት እሞክራለሁ፡፡ ነገር ግን ሚዛንን መጠበቅ ማለት ሁልግዜ ሌሎች እንደሚረዱት አይደለም፡፡በተለይም ከዋልታ ረገጥ ጠስሜት መለዋወጥ ጋር ለሚኖር ሰው ይህ እውነትነት አለው፡፡
ሳብራራው፡-ከ 18 አመቴ ጀምሮ ከዚህ ሁኔታ ጋር ኖሬያለሁ፡፡አሁን 37 አመቴ ነው፡፡የህክምና ባለሙያ ባልሆንም ወይም በዚህ ዙሪያ የለቅ ያለ ጥናት ባላደርግም፤የብዙ አመታት የህይወት ልምድና ተሞክሮ ግን በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ መረዳት እንዲኖረይ አድርጓል፡፡
እኔ ዋልታ ረገጥ የስሜት መለዋወጥን በሁለት ስያሜዎች እጠራቸዋለሁ፡-
የሁለት ጽንፎች ህመም
የባራችዮች ህመም
የሁለት ጽንፎች ህመም
ዋልታ ረገጥ የስሜት መለዋወጥ በከፍተኛ የስሜት ከፍታና ዝቅታ መዋዠቅ የሚገለጽ ነው፡፡ይህ በደስታና በሀይል መሞላት የታጀበ የስሜት ከፍታ ማኒያ ወይም ሀይፖማኒያ (mania or hypomaniya) ሲባል በተቃራኒው ሲሆን ደግሞ ከፍተኛ የስሜት መቀዝቀዝና እስከ እራስን የማጥፋት ስሜት ውስጥ መግባት ደረጃ ሊያደርስ ይችላል፡፡
ህክምናው ለምን አስፈለገ? ህክምናው እነዚህን ሁለት ጽንፎች ለማለዘብ ያግዛል፡፡የታወቀ መድሀኒት የሌለውና እስከዘላቂው የሚድን ባይሆንም ሁኔታውን ለመቆጠጠር ግን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡በተጨማሪም ህክምናውን በጥንቃቄ መከታተል የሂደቱ ዋነኛው አካል ነው፡፡
በዚህ ዋልታ ረገጥ የስሜት መለዋወጥ ውስጥ እንዳለሁ በህክምና ካወኩ ጀምሮ ለ 6 አመታት ምንም አይነት ህክምናን አልተከታተልኩም ነበር፡፡ይልቁንም ችግሩን በመንፈሳዊ አካሄድ ብቻ ለመረዳት እፈልግ ነበር፡፡ሰዎች ግን በህክምና ላይ መተማመን በእግዚአብሔር ላይ ያለኝን እምነት እንደመጠራጠር አድርገው የወስዱታል፡፡በዚህ ምክንያት እያንዳንዱ የህይወቴ እንቅስቃሴ በከፍተኛ የስሜት ከፍታና ዝቅታ ውስጥ የተሞላ ነበር፡፡
ዛሬም ተግዳሮቶቹ ቢኖሩም በህክምና እርዳታና በጠንካራ ክርስቲያዊ እርምጃዎቼ የተሻለ ሁኔታ ላይ እገኛለሁ፡፡እስካሁን የመጣሁበት መንገድ ታዲያ እምነትና ተቋማዊ ህክምና የማይጣረሱና በጋራ ማስኬድ እደሚቻል ተገንዝቤያለሁ፡፡
ለእናንተ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ላልሆናችሁ ሰዎች ሁኔታውን ለማስረዳት ሊከብድ ይችላል፡፡ስሜትን መቆጣጠርና ማስተናገድ የእለት ተለት ከባድ ተግዳሮት ነው፡፡እናም የማበረታታችሁ ነገር ቢኖር፣በስሜት መዋዠቅ ያለ ሰው ሲያጋጥማችሁ ወዲው ከመፈረጅ ይልቅ በርህራሄ መረዳትን አስቀድሙ፡፡ምክንያቱም ያ ግለሰብ ምን አይነት ህይወትን እያሳለፈ እንዳለ በፍጹም አናውቅምና፡፡
የባለራእዮች ህመም
ለምድነው የባለራእዮች ህመም ብዬ የጠራሁት?
ከአመታት በፊት ሰዎች ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር እንደሌለ የነግሩኝ ነበር፡፡እነዛ የሚነገሩኝ ቃላት ታዲያ በውስጤ ነበሩ በተለይም በማኒያ ስሜት ውስጥ በሆንኩበት ግዜ ምንም ነገር እንደማይገድበኝ ይሰማኛል፡፡የማኒያ ስሜት የማይቻለውን እንደሚቻል ያስመስለዋል፣የፈጠራ ችሎታን ይጨምራል፣ራእያችን የሆናል የሚል የንካራ እምነትን የፈጥራል፡፡
በእንደዚ አይነት የስሜት ከፍታ ውስጥ ወይም በዋልታ ረገጥ የስሜት መለዋወጥ ውስጥ ያሉ ሰዎች በዙውን ግዜ በትልቁ ያልማሉ፡፡ሌሎች ችግሩ ላይ ሲያተኩሩ እኛ ግን የአቅማችን ብቁነት ነው የሚታየን፡፡ሌሎች አይቻልም ብለው የሚያስቡትን ሁኔታ የመተለምና በድፍረት የማድረግ ስሜት ይሰማናል፡፡ይህ ስሜት ነው በዚህ ህመም ውስጥ የተደበቀው ስጦታ፡፡
ነገር ግን ዋጋ ያስከፍላል፤በማንያ ውስጥ የምናደርጋቸው ውሳኔዎች በአግባቡ ካልተመረመሩ የረጅም ግዜ መዘዝን ሊያስከትሉ ይችላሉ፡፡ለዚህም ነው ሁኔታችንን ሊረዱ፣ሊያግዙ እና የስሜታችንን መዋዠቅ ሊያረጋጉ የሚችሉ ሰዎች በዙሪችን መሆናቸው በጣም ወሳኝ የሆነው፡፡
እንደዚ አይነት ሰዎች በህይወቴ ስላሉ እግዚአብሔር ባርኮኛል ብዬ አስባለሁ፡፡ የውስጤን ይረዱኛል፤ያ እኔ ብቻ ነኝ የሚለው ስሜት ሲሰማኝ እንኳን በትህትና እንድራመድ ይስጹኛል፡፡እነርሱ ከፍታዬን፣ ዝቅታዬን እና ራእዬን አይተዋል እናም በዚህ ሁሉ ከእኔ ጋር ቆመዋል፡፡
ትልቁ ስእል
አዎ፣ ዋለታ ረገጥ የስሜት መለዋወጥ የህይወት ዘመን ሁኔታ ነው፡፡ነገር ግን በዚህ ሁኔት ውስጥ ማበብ ይቻላል፡፡እናም አሁንም ለሙሉ ፈውስ እያመንኩና እየጸለይኩ ፤የህንን ግን አውቃለሁ፡፡በአሀኑ ታሪኬ ውስጥ አግዚአብሔር እየከበረ ነውና፡፡በዚህ ህመም ውስጥ ካላችሁ ብቻችሁን አይደላችሁም፡፡ተጋላጭም ባለራእዮችም ልትሆኑ ትችላላችሁ፡፡ሚዛናችሁን መጠበቅ ትችላላችሁ፤በሌሎች ጫማ ውስጥ በመሆን ሳይሆን ለእናንተ የሚሰራውን የራሳችሁን ትርታ በማዳመጥ ነው፡፡
በጉዞዋችሁ ውስጥ ውበት አለ፡፡
በታሪካችሁ ውስጥ ጥንካሬ አለ፡፡
በመንገዳችሁም አላማ አለ፡፡


Comments