top of page
Untitled design (5).jpg

መልእክት ለቤተክርስቲያን

  • Writer: Naomie Deborah Tilahun
    Naomie Deborah Tilahun
  • May 12
  • 1 min read

መልእክት ለቤተክርስቲያን

በ ናሄሜ ዲቦራ ጥላሁን

ለተወደዳችሁ የቤተክርስቲያን ቤተሰቦች


የህን መልእክት የምጽፍላችሁ ጥቂት ሰዎች እነደማይረዱት ሁሉ፣ ክርስቶስን እንደተወ ሰው ሳይሆን በወጀብ መሀል ከክርስቶስ ጋር እንደተጣበቀ ሆኜ ነው፡፡በዚህ ወጀብ ውስጥ ሆኔ አንኳ የአይምሮ ህመምተኛ የመባልን ከባድ ጫና ተሸክሜው እገኛለሁ፡፡አለም በዚህ መልኩ ብትፈርጀኝም  እንኳ የእግዚአብሄርን ጣቶች ግን አለቀኳቸሁም፡፡ምክንያቱም የኔ ትክክለኛ ማንነት በሱ በክርስቶስ ብቻ የሚገለጽ መኆኑን አውቃለሁ፡፡


የመዝሙረኛው ዳዊት (44፣20-21) ቃላቶች የልቤን ጩኸት ያስተጋባሉ፡-

የአምካችንን ስም ረስተን ቢሆን እጃችንንም ወደ ሌላ አምላክ አንስተን ቢሆን እግዚአብሔር ይህንን አይመረምርም ነበርን?እርሱ ልብ የሰወረውን ያውቃልና፡፡


ይህ ቃል የኔ እውነታ ነው ደግሞም እግዚአብሔር የልቤን ያውቀዋል፡፡እርሱ ፊቴን በፍጹም ወደ ሌሎች አማልክት እንደማላማትር በእርግጥ ያውቀዋል፡፡በጨለማና ግራ በመጋባት ግዜያቶቼ ውስጥ ሁሉ ሌሎች በእግዚእሄር ላይ ያለኝን እምነት ቢጠራጠሩም እንኳን  እኔ ግን መሸሸጊያዬ ከሆነው ወደ አምልኬ መጸለይን አላቆምኩም፡፡የምናገረውን ሌሎች በቅጡ ባይረዱኝም ሌቤ ግን ወደ እሱ መቃተትን አላቆመም፡፡


በሁለንተናዬ ለክርስቶስ ያለኝን ፍቅር እንድትረዱኝ እሻለሁ፡፡ያጋጠሙኝ ተግዳሮቶች ከጌታ እየሱስ ጥላ ስር እንድርቅ አላደረገኝም፡፡ እዲያውም ይበልጡኑ ወደ እሱ እንድቀርብ አድርጎኛል፡፡በሌሎች ሰዎች የሚሰጠኝ ማንነትና መገለጫ ለኔ የሰማይ ፍርድ ሊሆኑ አይችሉም፡፡እኔ በእግዚአብሄር ዘንድ የተወደድኩ፣የተመረጥኩና ልጄ ብሎ የሚየራኝ ስለሆንኩ፡፡እኔም ከእርሱ ዘንድ አልራኩም እሱም በፍጹም ብቻዬን አልተወኝም፡፡


ወንድሞቼና እህቶቼ፣በማግለል መነጽር ሳይሆን በክርቶስ ጸጋ እንድተመለከቱኝ በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ፡፡ማንኛውም ህመም፣የሰዎች ስም መስጠትና በተሳሳተ መንገድ መረዳት ከእግዚብሔር ፍቅርና ከእየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ሊለየንና ሊያርቀን እንደማይችል እኔ ህያው ምስክር ነኝ፡፡


በዚህ አለም ስንኖር እያንዳንዳችን የራሳችን ውጊያ ቢኖርብንም በርህራሄ መንፈስ አንደ አንድ አካል ሆነን እጅ ለእጅ ተያየዘን እንድንቆም ይሁን፡፡የልብን ሚስጥር ከሚያውቀው፣እሱን ዘወትር እንደምንሻ


ከሚረዳን ከእግዚአብሄር አይናችንን ላፍታም እንዳንነቅል ይሁን፡፡

ከፍቅርና ከጸና እምነት ጋር

Recent Posts

See All
ጡብ በጡብ ላይ፡-ከእግዚአብሔር ጋር የአይመሮ ጤናን መገንባት፡፡

በ ናሄሜ ዲቦራ ጥላሁን አንድ ግንበኛ በትዕግስት የተሞላ ባለሙያ ነው፡፡ ጡቦቹን አንድ በአንድ በጥንቃቄ እና በእርጋታ ይደረድራቸዋል፡፡ የሚገነባው መዋቅር ጠንካራና የተረጋጋ መሆኑን እርግጠኛ ይሆናል፡፡ለምን? ምክንያቱም ጡቦቹን መደርደር ብቻ ሳይሆን ቤትን ነው እየገነባ ያለው፤ ለብዙ ዘመናት የሚቆይ በሀይለኛ ንፋስ

 
 
 
ዋልታ ረገጥ ጠስሜት መለዋወጥ:-የሁለት ጽንፎችና የባለራእዮች ህመም

በ ናሄሜ ዲቦራ ጥላሁን አብዛኛውን ግዜ እንደ አንድ ከአይምሮ መታወክ ሁኔታ ጋር እንደሚኖር ሰው ሆኜ ስመለከተው ብዙ ሰዎች ሚዛንን መጠበቅ ብለው የሚጠሩትን ሀሳብ ለማግኘት እሞክራለሁ፡፡ ነገር ግን ሚዛንን መጠበቅ ማለት ሁልግዜ ሌሎች እንደሚረዱት አይደለም፡፡በተለይም ከዋልታ ረገጥ ጠስሜት መለዋወጥ ጋር ለሚኖር ሰው

 
 
 

Comments


bottom of page