top of page
Untitled design (5).jpg

ጡብ በጡብ ላይ፡-ከእግዚአብሔር ጋር የአይመሮ ጤናን መገንባት፡፡

  • Writer: Naomie Deborah Tilahun
    Naomie Deborah Tilahun
  • Jun 24
  • 2 min read




በ ናሄሜ ዲቦራ ጥላሁን


አንድ ግንበኛ በትዕግስት የተሞላ ባለሙያ ነው፡፡ ጡቦቹን አንድ በአንድ በጥንቃቄ እና በእርጋታ ይደረድራቸዋል፡፡ የሚገነባው መዋቅር ጠንካራና የተረጋጋ መሆኑን እርግጠኛ ይሆናል፡፡ለምን? ምክንያቱም ጡቦቹን መደርደር ብቻ ሳይሆን ቤትን ነው እየገነባ ያለው፤ ለብዙ ዘመናት የሚቆይ በሀይለኛ ንፋስ የማይናጋ ቤትን ነው የሚገነባው፡፡


ከመንፈስ ጭንቀት፣ ዋልታ ረገጥ  የስሜት  መለዋወጥ ጋር ለሚታገሉ ሰዎች፤ አዕምሯችንን፣ ስሜታችንን ለማሻሻልና ለማበልፀግ ከላይ ያሥቀመጠጥኩት ፍሬ ሀሳብ ጥሩ ይመስለኛል፡፡ሰላምን እና ፈውስ ወይም ድነት ጌዜን ይፈልጋሉ፡፡ ከእግዚያብሄር ድጋፍ ጋር ግን ጡቦቹን እንድ በአንድ በማስቀመጥ የፀና ግንብን መገንባት እንችላለን፡፡


ሙሉ በመሆን በፍፁም አልተሰበርንም፡፡


ሲጀመር፤ ለእግዚያብሔር ህይወታችሁን በትርምስ የተሞላ አይደለም፡፡ በማንኛውም ህመም፣ አስተሳሰብ ወይም የህክምና ሆኔታ ውሰጥ ብትሆኑ፤ ለፈውሱ እጁ  አያጥርም፡፡ነገሮችን እንደነበሩ ያደርጋል፡፡ በተጎዳችሁባቸው ነገሮች ላይ እንደገና እንድትቆሙ ይረዳችኋል፡፡ 


ትንቢተ ኤርሚያስ 30፡17፣ እንዲህ ይላል፡- ጠላቶቻችሁ ጽዮን እንደ ተጣላችሁ መቅረቷ ነው፤ የሚጠነቀቅላት የለም ቢሉም ፤እኔ ጤንነታችሁን እነደገና እመልስላቸሁኃለሁ፤ቁስላችሁንም እፈውስላችሁዋለሁ፤እኔ እግዚያብሄር ይህን ተናግሬያለሁ


እግዚያብሔር በልባችንና በአዕምሯችን በዚህ መንገድ ነው የሚሰራው ስለዚህም በህይወታችን የሚያጋጥሙን ሁኔታዎች፣የስሜት ቀውሶች እና የአዕምሮ ህመም ተቋቁመን እንደገና እንድንቆም ይረናዳል፡፡


ጡብ አንድ፡-ሀቀኛ ሁን


ለማንኛውም ጥሩ የቤት መዋቅር ጠንካራ መሰረት የመጀመሪያው ነገር ነው፡፡ በምናልፍበት ሂደት ውስጥ ሀቀኛነት የመጀመሪያው ደረጃ ነው፡፡ ነገሮች ጥሩ እናዳልሆኑ እያወቅን ጥሩ እንደሆኑ ማስመሰል የለብንም፤ እውነቱን እግዚያብሄር ስለሚያውቅ፡፡


መዝሙረ ዳዊት 34፡18፣ ሲናገር "እግዚያብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ፤መንፈሳቸው ለተሰበረም ያድናቸዋል፡፡ "


ከልባችን ስንፈልገው እግዚያብሔር ቅርብ ነው፤ ያኔ ነው ፈውሳችን የሚጀምረው፡፡


ጡብ ሁለት፡- ሸክምን ማራገፍ


የአዕምሮ ጤና መታወክ እራሱን የቻለ ሸክም አለው፡፡ እናም ለብቻችሁ ጫናውን መሸከም የለባችሁም ፤ለእግዚያብሔር አሳልፋችሁ ስጡ፤ እርሱ ይረዳቸዋል፡፡


1ኛ ጴጥሮስ 5፡7፣ ሲናገር፣ ‘’እርሱ ስለ እናነንተ ያስባል እና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት፡፡’’ 


‘’ጌታ ሆይ ብቻዬን አልችለውም እርዳኝ’’ በሉት እርሱም ይረዳችኋል፡፡


ጡብ ሦስት፡-እራሳችሁን ተንከባከቡ፡፡


ፈውስ እራስን መግዛት እና መስራትን ይፈልጋል፡፡ ህክምና ማድረግ፣ ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት ከእግዚያብሔር ጋር ጊዜን ማሳለፍ ሊሆን ይችላል፡፡እያንዳንዳቸው ዋጋ አላቸው፡፡ የአዕምሮ መታወክን ለማሻሻል ግዜ የሚያስፈለግ ቢሆንም ያለማቋረጥ ከሰራችሁ ጥሩ ውጤትን ታገኛላችሁ፡፡


ሮሜ 12፣2 ሲናገር፡”የእግዚያብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ፤ ፍፁም የሆነውን ነገር ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአዕምሮችሁ መታደስ ተለወጡ፡፡’’


እግዚያብሔር ቀስ በቀስ በለውጣችሁ ላይ ያግዛችኋል፡፡ ወደፊት ቀጥሉ፡፡


ጡብ አራት፡ ብቻችሁን አትገንቡ፡፡


አንድ ጡብ በራሱ ብቻውን ምንም አይነት ጥንካሬ አይኖረውም፡፡ ጥንካሬ የሚሰጠው በዙሪያው ያሉ ጡቦች ናቸው፡፡ የኛም ህይወት እንዲሁ ነው፡፡ በዙሪያችን ድጋፍ ያስፈልገናል፡፡ከህክምና ባለሙያ፣ ታማኝ ጓደኞች ፣ ከአገልጋዮች፣ ከድጋፍ ቡድን ስብስቦች ጋር እራሳችሁን አቅርቡ፡፡


መፅሀፈ መክብብ 4፣9-10 ሲናገር "ከአንድ ሰው ሁለት ይሻላሉ፤አንዱ ቢወድቅ ሌላው ያነሳዋል፤ እናንተ ሸክም አይደላችሁም፤ ብቻችሁን አይደላችሁም ፤የተወደዳችሁ ናችሁ፡፡"


ጡብ አምስት፡ ተስፋ ሰንቁ፡፡


በመጨረሻም  በፈፅም ተስፋ እንዳትቆርጡ ፤ በቶሎ ውጤት ባታገኙም፣ ነገሮች አዝጋሚ ቢሆኑም፣ እግዚያብሔር ግን በስራ ላይ ነው፡፡እየገነባ ነው፡፡


ፊሊጲሲዮስ 1፣6 ሲናገር፡-“በእናንተ መልካም ስራ የጀመረውን እግዚያብሔር ስራውን ፈፅሞ እንደሚጨርሰው እርግጠኛ ነኝ፡፡እግዚያብሔር በውስጣቸው ቢሆን በዙሪያችሁ በስራ ላይ ነው፡፡”


የመጨረሻ  ላንቺ ለደከምሺው ሴት፣ የጠፋችሁ ለሚመስላችሁ ወጣቶች፤ ከአዕምሮ ጭንቀት ፣ድባቴ እና ከማንኛውም የአዕምሮ መታወክ ጋር ለምትታገሉ ፤ ጡቡን  አንድ በአንድ እያስቀመጣችሁ ነው፡፡ ጠንካራ ግንብን እየገነባችሁ ነው፡፡ ከእግዚያሔር እርዳታ ጋር ሰላማዊ ቤትን እየሰራችሁ ነው፡፡ ግዜን ውሰዱ፣


እራሳችሁን ከሌሎች መንገድ ጋር አታነፃፅሩ፡፡ብቻ ዝም ብላችሁ  በእርሱ እጅ ላይ ስትሆኑ ትጠነክራላችሁ፤ እየጨመራችሁም ትሄዳላችሁ ፡፡እርሱ ከእናነንተ ጋር ስራውን አልጨረሰምና፡፡

Recent Posts

See All
Brick by Brick: Building Mental Wellness with God

A bricklayer is patient. He takes his time to ensure that the structure he is constructing is sturdy and stable, he carefully places each brick, one at a time. Why? Because he's building a house, not

 
 
 

Comments


bottom of page