መፅሀፍ ቅዱስን ፣ፀሎትን እና ህክምናን፣ዋልታ ረገጥ የስሜት ድባቴን ለመቆጣጠር እንዴት እንደተጠቀሙበት፡፡

የዋልታ ረገጥ የስሜት መለዋወጥ ደረጃ 1 ምልክቶችን በ አስራዎቹ እድሜዬ መጨረሻ ላይ መታየት ቢጀምርም፣ በህክምና የተረጋገጠው ግን በሀያዎቹ መጀመሪያ ነበር፡፡ በግዜው አልፈበት ነበረውን የስሜት ቀውስ ምን ብዬ እንደምጠራው አላውቅም ነበር፡፡ የሆነ አይነት ችግር ውስጥ እንዳለሁ ግን አረዳ ነበር፡፡ ሁለቱንም የስሜት ከፍታና ዝቅታ፣በዚህኛው እራስን የማጣት ስሜት፣ በዛኛው ደግሞ የአይበገሬነት ስሜቶችን አስተናግድ ነበር፡፡ በተለይም እንደ አንድ አማኝ ሁኔታውን ለማውራት እንኳን እሸማቀቅ ነበር፡፡ ብቻ ግራ የሚያጋባ ነገር ነበር፡፡
አሁን እድሜዬ 37 ነው፡፡ ምንም እንኳን የፈውስ ሂደት አልጋ በአልጋ ባይሆንም፣ ተስፋ አለ የሚለውን ቀላል እውነት ለሁሉም ለማድረስ እፈልጋለሁ፡፡
ዋልታ ረገጥ የሥሜት መለዋወጥ እና ድባቴን ማስተናገድ ቀላል አልነበረም፡፡ በእግዚብሔር ፀጋ ግን፣ ከባድ በሚመስሉ ሁኔታዎች ውስጥ እንዳልፍ እያስቻለኝ፣ የዕለት ተዕለት የፈውስ ቁመናን እንዳገኘ አድርጎኛል፡፡ ይህ ቁመና ፀሎት ፣የመፅሀፍ ቅዱስ ንባብ እና የስነ-ልቦና ህክምናን ያካትታል፡፡
1. ፀሎት፡- ታማኝነትን ያገኙሁበት፡፡
አንዳንዴ በቆንጆ ቃላት ከመፀለይ ይልቅ አለቅሳለሁ ፣ እቃትታለሁ፡፡ ይሁን እንጂ ሮሜ 8፡26 ይህን ያስታወሰኛል፡፡
"እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፤ እንዴት እንድንፀልይ እንደሚገባን አናውቅምና፣ ነገር ግን መንፈስ እራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል"
በህወይቴ መስመር የማላስመስልበት ቦታ ቢኖር ፀሎት ነው፡፡ ጭንቀቴን፣ የስሜት ውጥረቴን፣ ሀሳቤን ሁሉ ወደ እርሱ አቀርባለሁ፡፡ በእግዚያብሔር መገኘት ውስጥ ግልፀነትንና እፎይታን አግኝቻለሁ፡፡
2. የስነ አእምሮ ህክምና፡- ያለ፣የእምነት ክህደት ያልሆነ፡፡
ለረጅም ግዜ፣ የአዕምሮ ህክምናን መፈለጌ፣ በእግዚያብሄር ላይ አለመተማመን እንደሆነ አምን ነበር፡፡ ነገር ግን፣ ፈውስና ጥበብን በጋራ መስኬድ እንደሚቻል ተገንዝቤያለሁ፡፡እናም አሁን በስነ-ልቦና ህምክና ምክንያት፣ ለስሜቶቼ ቃላትን አግኝቻለሁ፡፡ ስሜቴን የምቆጣጠርበትና ሰላሜን የምጠብቅበት ዘዴን አግኝቻለሁ
የስነ-ልቦና ህክምና፣ ሀሳቦቼን በቅጡ ማስተናገድ እንድችል እረድቶኛል፡፡ ይህ ግን የእግዚብሔርን ቦታ አይተካም፡፡
3. ህክምናን፡- በአግባቡ ማስተዳደር
ህክምናን መከታተል እንደ አንድ ህይወት አካል አድርጎ መቀበል በጣም የሚከብድ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ፣ በሀኪሞች የሚሰጠኝን ህክምና መከታተል በእምነቴ ላይ ጥርጣሬን አያመለክትም ይልቁንም የፈውስ መንገድ ነው፡፡ ህክምናውን በመከታተሌ ምክንያት ነገሮችን የመተግበር ችሎታን እንዳዳብር እና እንዳብብ እረድቶኛል፡፡
4. መፅሀፍ ቅዱስ፡- የነፍሴ መልህቅ
ስሜቶቼ ሊያታለልኝ ሲሞክሩ ወደ እግዚያብሔር ቃል እሄዳለሁ፡፡ የትንቢተ ኢሳያስ 26፣3 ምዕራፍ የምፈልገውን መረጋጋት ያስታውሰኛል፡፡
"በአንተ ላይ ታምናለችና በአንት ለምትደገፍ ነፍስ ፈፅመህ በሰላም ትጠብቃታለህ"
መፅሀፍ ቅዱስን በማነብ ግዜ ማስታወሻ እይዛለሁ፡፡ ድንዛዜ በሚሰማኝ ግዜ ከመዝሙረ ዳዊት ምእራፎች ጮክ ብዬ አነባለሁ፡፡ የእግዚያብሔር ሰው የሆነው ዳዊት እንኳን በከባድ ድባቴ ወስጥ ያልፍ ነበር ነገር ግን እግዚአብሔርን አልተወውም፡፡ ይህን ለእራሴ አስታውሳለሁ፡፡
አሁንም ከባድ ቀናት ያጋጥሙኛል፡፡ አንዳንዶቹ ጠዋቶች ከሌሎቹ በጣም ይከብዱ ነበር፡፡ ነገር ግን ፈውስ የፈፁምነት ጉዳይ ሳይሆን የቀስ በቀስ እድገት ጉዳይ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ፡፡በተጨማሪም፣ ህይወትን የመኖር፣ በኢየሱስ ላይ የመደገፍ፣ ጥሩ ባልተሰማን ግዜ በማይታመን ሁኔታ መወደዳችንን የመረዳት ጉዳይ ነው፡፡
ይህን የምታነቡ ሴትም ብትሆኚ ወጣት ብቻችሁን አይደላችሁም፡፡እግዚያብሔር ተግዳሮቶቻችንን ያውቃቸዋል፣ እርሱ በህመማችን አይሸማቀቅም፡፡ በሸለቆ ውስጥም ቢሆን እርሱ ከእናንተ ጋር ነው፡፡
በተደጋጋሚ እንደገና ለመቆም የምንችልባቸውን መንገዶች ያቀርብልናል፡፡እነዚህም መንገዶች፡-
ፀሎት፣የምክር አገልግሎት፣ህክምና ፣መፅሃፍ ቅዱስና በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎች ናቸው፡፡


Comments