top of page
Untitled design (5).jpg

በቃልኪዳኑ መፈጸም ውስጥ የአርሱ ውለታ

Writer: Naomie Deborah Tilahun
Naomie Deborah Tilahun
Aug 3
2 min read



የመፅሀፍ ቅዱስ መሰረት


"እግዚያብሔር ለአብርሀም ተገልጦ፣ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ" አለው (ዘፍጥረት 12፣7፤15፣18-21)፡፡

"እግዚያብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለእስራኤል እንዲዋጉ ልባቸውን ያደነደነው ከእግዚያብሔር ዘንድ ነበር (እያሱ 11፣20)”፡፡



የእግዚያብሔር ቃልኪዳን እና የኔ ጉዞ


በእያሱ 11፤20 ያለውን ቃል ሳነበው፣ከእስራኤላውያን ተጋድሎ በላይ ነው የምረዳው፡፡የራሴ ህይወት የሚታየኝ፡፡ የእግዚያብሔር ቃልኪዳን እኔ ላሳካው ከምችለው በላይ ትልቅ ሆኖ ነው የሚታየኝ፡፡


 ሁኔታዎቼን በማየት እንዲህ ያልኩባቸው ግዜያት ነበሩ "እግዚያብሔር በልቤ ያስቀመጠውን ለማድረግ በቂ ጉልበት ፣ልምድ እና ግብዓቶች የሉኝም"


ልክ እንደ እስራኤላዊያን ሁሉ፣ ከተጋፈጥኳቸው ግዙፋን ይልቅ ትንሽነት ተሰምቶኛል፤ከዋልታ ረገጥ የስሜት መለዋወጥ፣ የአዕምሮ ጭንቀት ትግል ጋር ይሁን ወይም ለመቋቋም ከሚከብድ እግዚአብሔርን የመጠበቅ ሁኔታ ውስጥ መሆን፡፡ እንደዛም ሆኖ እርሱ ለእስራኤላውያን እንደተዋጋው ሁሉ ለእኔም በዝምታ ሲዋጋልኝ አይቼዋለሁ፡፡ የቆምኩበት የከዳኘ በመሰለኝ ግዜ እንኳን፣ከመጋረጃው በስተጀርባ የድሌን መንገድ እያስተካከለልኝ ነበር፡፡



ሞገስ ስለእኔ ሳይሆን ስለእርሱ


እስራኤላውያን ከነዓንን የወረሱት ጠንካራ ጦር ስለነበራቸው ሳይሆን የእግዚያብሔር ቃልኪዳን ስለነበራቸው ነው፡፡ የኔም ታሪክ እንደዚሁ ነው፡፡


ያሉኝ ህልሞች፣የህይወት ጥሪ እና የተረዳኋቸው የውስጥ ፈውስ እንኳን ከእኔ ጥንካሬ የሆኑ አይደሉም፡፡እርዳታ ማለት የህይወቴ እውነታና ተግዳሮቶች በአንዴ  ይጠፋሉ ማለት እንዳልሆነ መማር ነበረብኝ፡፡ይልቁንም የእግዚያብሔር ሀይል በህይወቴ መገለጥና የእርሱ ቃል ለውጤቱ ዋስትና መሆኑ ነው፡፡


በሆስፒታል ውስጥ እያነባሁ በምፀልይባቸው ግዚያት፣አእዕምሮዬ እረፍት የለሽ በሆነበት ግዜ እና ውስጤ ግልፅነት በፈለገባቸው ግዜያት የእርሱ እርዳታ ከእኔ ጋር ነበር፡፡ሁልግዜም የእርሱ ቃልኪዳን ከእኔ ህመም የበለጠ ነው፡፡



እርግጠኛ የሆንኩበት ውጤት


ወደኃላ ዞር ብዬ ሳየው፣መሰበር የነበረብኝ ቅፅበቶች ነበሩ ነገር ግን፣ የእግዚያብሔር አርዳታ አቁሞኛል፡፡ ጠላቶቼ ሊሰብሩኝ በሞከሩ ግዜ እርሱ ግን ድሌን እየፃፈልኝ ነበር፡፡ ታሪኬ ማብቃት በነበረበት ግዜ፣በቃልኪዳኑ አሳልፎኛል፡፡


በህይወቴ ላይ ያየሁት ውጤት የተረጋገጠ እንደነበረ አሁን ተገንዝቤያለሁ ፡፡እግዚያብሔር ቃል በገባልኝ ቅፅበት ለኔ የተረጋገጠ ነገር ነበር፡፡ እያነከስኩም ቢሆን እንኳን ወዳስቀመጠልኝ ስኬት ወደ  ፊት መቀጠል  ብቻ የነበረብኝ፡፡



የሙጥኝ ያልኩት ቃል


በመንገዴ ላይ ጌታ በጆሮዬ እንዲህ ሲል እሰማዋለሁ፡-


ናሆሜ፣ ቃልኪዳኖቼ አይታጠፉም፤ አንቺ ላይ የምስራውን አልጨረስኩም ፡፡ በተጋፈጥሽባቸው ጦርነቶች ሁሉ ምንም ያህል እጆቼ ብርቱ እንደነበሩ አሳይቶሻል፡፡ የፊትለፊትሽን በጎደለሽ ነገር ላይ ሳይሆን በምትናገሪው ቃል ላይ መዝኚ፡፡እርዳታ ማለት፣ ማድረግ ስለምትችይው ነገር ሳይሆን ስላደረኩልሽ ነገር ማለት ነው፡፡ቃል በህይወትሽ ውሰጥ ሲፈፀም ታያለሽ፣ ምክንያቱም ላንቺ  የገባሁት ቃልኪዳን ስለማይሰበር፡፡

Recent Posts

See All
Favor Through Fulfillment of Promise

Scripture Foundation “God had promised Abraham, Isaac, and Jacob that their descendants would inherit the land of Canaan.” (Genesis 12:7; 15:18–21) “For it was the Lord himself who hardened their hear

 
 
 

Comments


bottom of page