top of page
Untitled design (5).jpg

ከስሜት ቀውስ ወደ ድል፡-እንዴት እምነት በድህረ አሰቃቂ ሁኔታ የአእምሮ ሁከት ውስጥ እንዳሳለፈኝ

Writer: Naomie Deborah Tilahun
Naomie Deborah Tilahun
Aug 3
2 min read



ድህረ አስቃቂ ሁኔታ የአእምሮ መታወክ በህይወቴ ካጋጠሙኝ ከባድ ሁኔታዎች ዋነኛው ነው፡፡


በሀያዎቹ እድሜ እያለሁ በሰውነቴ እና በአዕምሮ ላይ ዘላቂ ጠባሳ ያሳረፈ ፆታዊ ጥቃት ደርሶብኘ ተወጥቼዋለሁ፡፡ ለዓመታት በዝምታ ውስጥ ይህንን ጉዳት ተሸክሜዋለሁ፡፡ መጀመሪያ የድህረ አሰቃቂ ሁኔታ የአዕምዬ መታወክ በገጠመኝ ግዜ ምን እየተካሄደ እንደሆነ አልተረዳሁትም ነበር፡፡ በተለመዱ የለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች ውስጥ፣ ቅፅበታዊ ምልሰት ትውስታዎች ወደ አዕምሮዬ እየመጡ ነበር ሁኔታዎቹ የጀመሩት፡፡ ልብሶቼን እያስተካከልኩ ሳለሁ በድንገት ያሳለፍኩት የጥቃት ሁኔታ ፌቴ ላይ ድቅን ይልብኝ ነበር፡፡ በድንገትም ድርቅ ብሄ እቀር ነበር፡፡ ሁኔታው የሚያልፍ እየመሰለኝ ዝም እል ነበር፤ ግን  አልሆነም፡፡ ከምርመራ ውጤት በኋላ ያለውን ሁኔታ እያስተናገድኩ ሳለሁ ነው ምልሰቶቹ ዋልታ ረገጥ የስሜት መለዋወጡ ቀውስ የተቀሰቀሰው፡፡በዚህ ቀውስ ምክንያት የተከሰቱብኝ የስሜት መወጠርና እና የእንቅልፍ እጦት ወደ ከፍተኛ የስሜት ከፍታ እና ዝቅታ ከመክተትም አልፎ ሆስፒታል ያስገባኝ ነበር፡፡ ሀኪሞች፣ የቅርብ ወዳጆቼ ለምን በዚህ በማያቆም ቀውስ ውሰጥ እናዳለሁ አልገባቸውም ነበር፡፡ ነገር ግን ሁኔታው ከዋልታ ረገጥ የስሜት መታወክ የዘለለ ነበር፤የሆነ ጠለቅ ያለ ነገር፡፡


ከአመታት በኃላ፣ ለስነ-አእምሮ ሀኪሜ ስለ ምልሰቶቹ ነግሬው ነበር፡፡ ሁኔታው ድህረ አሰቃቂ የአእምሮ መታወክ እንደሆነ ቢያስረዳኝም ነገሩ ግን እንደዛ እናዳልሆነ ያወኩት ሌላ የስነ-አዕምሮ ሃኪም ጋር ምርመራ ካደረኩኝ በኋላ ነበር፡፡ ወደ ሙሉ ህክምና ከመግባቴ በፊት ሀኪሙ ሁኔታዎቹንና ምልክቶቹን በጥልቀት አስረድቶኝ ነበር፡፡ እንዴት ሁኔታዎችን መቋቋም እንደምችል ማወቅ  ነበረብኝ፡፡ ልዩ የህክምና መርሀግብር ስጀምር ቀስ በቀስ ነገሮች መሻሻል ጀመሩ፡፡


ዛሬ፣እነዚያ ምልሰቶች በቀላሉ አይከሰቱም ወይም የሉም ማለት ይቻላል፡፡እናም የስሜት ቀውሱን እንዴት መቆጣጠር እንዳለብኝ በህክምና እርዳታ ሳይሆን በእምነት ውስጥ ተምሬያለሁ፡፡



የፀሎት ጉልበት


በመጣሁበት መንገድ ሁሉ ፀሎት ትልቁ የፈውስ ምንጭ ነበር፡፡ የስሜት ቀውስ ሲፈጠር ፀሎት ያረጋጋኛል፣ ትኩረቴን ከህመም ወደ ሰላም ይመልሳል፣ ከሆነብኝ ነገር ይልቅ በመስቀል ላይ ለኔ የሆነልኝን እንዳስብ ያደርገኛል፡፡


በመንፈሳዊ ጦርነት አምናለሁ፣ እናም መታጠቅ አለብን፡፡ ኤፌሲዮን 6 እንሚለው፣ ከእግዚያብሔር ዕቃ ጦር ጋር፣ እኔ የጀመርኩት ያለማቋረጥ በመፀለይ ነው፡፡ ፀሎት ለእኔ ከእግዚያብሔር ጋር መነጋገር ብቻ ሳይሆን ከፈጠረኝ አምላክ ጋር የመገናኘት ጉዳይ ነው፡፡ ያ ግንኙነት በምንም የማይገኘውን ሰላም ይሰጠናል፡፡


ህመሜን ብቻዬን  መሸከም እንዳሌለብኝ ማወቅ በራሱ ነፃነትን የሚስጥ ነው፡፡ሁሉን ወደ እግዚያብሔር ሳመጣው እረፍትን አገኛለሁ፣እተነፍሳለሁ፡፡


እምነት ሁሌም መልስ ላይሰጠን ይችላል ነገር ግን ሁሌም የእርሱን መገኘት ያረጋጥልናል፡፡


 ሰዎች ይጠይቁኛ፣ ‘’ለሆነብሽ ነገር እግዚብሔርን ትወቅሺዋለሽ?’’


ከዚህ ጥያቄ ጋር ታግያለሁ፣ አልቅሻለሁ፡፡ “የት ነህ እግዚያብሔር ሆይ?  ለምን እነዚህ ነገሮች አታቆምልኝም?” 

ለሁሉም መልስ ባይኖረኝም፣ ይህንን ግን አውቃለሁ፡፡ እግዚያብሔር አልተወኝም፡፡በነገሮች አሳልፎኛል፤ በዚህ ብቻ ለእግዚያብሔር ክብር ይገባዋል፡፡


 ዛሬ "የት ነበርክ ጌታዬ?" ብዬ መጠየቅን ትቻለሁ፡፡ ይልቁንም "ሰለተሸከምከኝ አመሰግናለሁ" ነው የምለው፡፡

ይህ የእይታ ለውጥ፣ ይሆናል ብዬ የማላስበውን ፈውስ ሰጥቶኛል፡፡



አሁንም በትግል ላይ ላላችሁ


አሁንም ከድሀረ አሰቃቂ ሁኔታ የአዕምሮ መታወክ እና ከስሜት ቀውስ ሁኔታ ጋር እየተፋለማችሁ ከሆነ ብቻችሁን አይደላችሁም፡፡ ፈውስ እውነት ነው፣ ይቻላል ፤ተስፋ አለ፡፡በአንድ ለሊት ላይሆን ይችላል ነገር ግን በእርግጥ ይመጣል፡፡ በትክክለኛ ድጋፍ ፤ህክምና፣በዋነኝነት ደግሞ ከእምነት ጋር ሙሉ መሆን ትችላላችሁ፡፡


አሁንም ቢሆን ለሙሉ ፈውስ እፀልያለሁ፡፡ አሁንም እንኳ በመሀል ሁኔታ ላይ ሆኜ እግዚያብሔር ታሪኬን ለእርሱ ክብር እንደሚያደርገው አምናለሁ፡፡ እነዛ ከባድ ሁኔታዎቼን ወደ  ምስክርነት ፣ ህመሞቼን ደግሞ ወደ አላማዎቼ ይቀየራቸዋል፡፡ ወደ ፊት ቀጥሉ፣ ፀሎት አታቁም፣ በእምነታችሁ ቀጥሉ፣ እርሱ እያሳረፋችሁ ነው፡፡

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page