እግዚአብሔርና ጭንቀት፡-ጭንቀታምም ሆኜ ክርስቲያን መሆን እችላለሁ?

ሀቁን ስትጋፈጥ፣ ብዙ ወጣቶችና ሴት ክርስቲያኖች በዝምታ ውስጥ ከዚህ ጥያቄ ጋር ይታገላሉ፡፡ “ክርስቶስን ከወደድኩ ዘንዳ ስምን በስጋት ውስጥ እሆናለሁ?”
በእርግጥም የህን ጥያቄ ልባችሁ በከበደባችሁ ግዜ፣ በአምልኮ ላይ ሆናቸሁ እራሳችሁን ጠይቃችሁ ይሆናል፤ወይም በለሊት እያነባችሁ፡፡ እንድዲህ ከሆነ ፣በራሳችሁ ብቻ አይደላችሁም፡፡ እውነታውን ስናይ፣ ክርስቲያን መሆን ጭንቀታችሁን ለመርሳት ከመሞከር ይልቅ በክርስቶስ ላይ እንድትጥሉት ይጋብዛችኃል፡፡
የእግዚያብሔርን ሀሳብ የሚከተለው ዳዊት በመዝሙር ዳዊት 94፣19 እንዲህ ይላል፡-
"የውስጤ ጭንቀት በበዛ መጠን፣ ማፅናናትህ ነፍሴን ደሰ አሰኛት"
ሙሉ ሰው እና አምላክ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ እራሱ፣ በጌተሰማኒያ የጭንቀት ሸክም ተሰምቶት ነበር፡፡ በሉቃስ 22፣44 እንደሚናገረው፡- “የደም ላብ እስከሚያልበው ድረስ እርሱ ክርስቶስ በጭንቀት መንፈስ ውስጥ ነበር”
ላፍታ ይህን እናሰላስል፡፡ ክርስቶስ ከአቅም በላይ የመሆን ስሜትን ተረድቶታል፡፡
እምነታችሁ በጭንቀት አይረጋገጥም ፣ይልቁንም በእርሱ ላይ በመደገፍ ያጠነክራችኋል፡፡
“ለሚያስብለህ ለሱ ሀሳብህንና ጭንቀትህን ተወው"(1ኛ ጴጥሮስ 5፣7)
አስደሳቹ ነገር በጭንቀት ውስጥ መሆናችን ነው፡፡ እግዚያብሔር በእናንተ ተስፋ አይቆርጥም፡፡ ፍፁምነትን ሳይሆን ሰላምን ይሰጣችኋል፤በቸልተኝነት ሳይሆን በትግልና በተግዳሮቶች መካከል በቀጥታ የሚያገኛችሁ ሰላም፡፡
እናም ክርስቲያን ሆኖ ከጭንቀት ጋር መታገል ይቻላል፡፡ ይሁንና፣ክርስቶስ ስላለ ይህን ውጊያ ብቻችሁን መዋጋት የለባችሁም፡፡
ቆም ብላችሁ አስቡ፡፡ ልባቸው በከበደባቸው እግዚያብሔር በጭንቀት ውሰጥ ላሉ ቅርብ ነው፡፡ እርሱ፣ በመልስ ፍለጋ ውስጥ መደላድል፣ በትርምስ ውስጥ መረጋጋት፣ በወጀቡ መሀል ፀጥታ የሆንላችኋል፡፡
በተግዳሮት ውስጥ ካላችሁ አናንተ መጥፎ ክርስቲያን አይደላችሁም፡፡ አናንተ በእግዚያብሔር እጆች ላይ ማረፍን ያወቃችሁ ክርስቲያኖች ናችሁ፡፡ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይቅርታን የሚያደርግ እና በርህራሄ የሚፈውስ እግዚያብሔር ላይ መመካትን እየተማራችሁ ነው፡፡


Comments