top of page
Untitled design (5).jpg

መጣላት ወይም መታገል፡- ከእግዚያብሔር ጋር ለመታገል የላችሁ ቁመና፡፡

  • Writer: Naomie Deborah Tilahun
    Naomie Deborah Tilahun
  • Aug 3
  • 2 min read




መፅሀፍ ቅዱሳዊ ትኩረት


"ያዕቆብም ብቻውን ቀረ፤ሰውም እስኪነጋ ድረስ ከእርሱ ጋር ታገለ፡፡” (ዘፍጥረት 32፣24)



መንፈሳዊ ንባብ


ከእግዚያብሔር ጋር በመጣላትና በመታገል መካከል የተቀደሰ ልዩነት አለ፡፡ ሁለቱም ጠንካራና ስሜታዊ ናቸው፡፡ሁለቱም እንባን ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡ አንዱ ልብ ሲያደነድን ሌላው ደግሞ ይፈወሳል፡፡


 እራሴን ከእግዚያብሔር ጋር በመጣላት ውስት ሳገኘው ፣ብዙውን ግዜ በእንቢተኝነት ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡ የሚናገረኝን መስማት አልፈልግም ነበር፣ በተለይም የእርሱ ምሬት ከእኔ መሻት ጋር ሳይገኛኙ ሲቀር፡፡ ከእርሱ ግዜና አካሄድ፣ ከዝምታው ሳይቀር እጣላ ነበር፡፡ ከእግዚያብሄር ጋር መጣላት ግድግዳን እንደመግፋት ነው፣ጉልበት መጨረስ ግን ግድግዳው ፈቀቅ አይልም፡፡


ዮናስ ይህን ስሜት በደንብ ያውቀው ነበር፡፡ እግዚያብሔር ወደ ነነዌ ሲጠራው እርሱ ግን በተቃራኒው መንገድ ወደ ሰሜን ነበር የሄደው፡፡ ለምን? ምክንያቱም ከእግዚያብሔር እቅድ ጋር አልተስማማም፡፡ እግዚያብሔር ትክክል እንዲሆን ይፈልግ ነበር፣እግዚያብሔር ግን ምህረትን እያደረገለት ነበር፡፡ከእግዚያብሔር ጋር መጣላት ማለት ለእርሱ ከመታዘዝ ይልቅ የራሳችሁን አመለካከት ማስበለጥ ማለት ነው፡፡


ግን ደግሞ አንዳንድ ቅጽበቶች አሉ፤እምቢ የማለት ሳይሆን ይልቁንም መታገል፡፡ በጵንኤል፣ የያእቆብ ለሊት እንቢተኝነት አልነበረም፣ ይልቁንም ተስፋ የመቁረጥ እንጂ፡፡ ከእግዚያብሔር ለመሸሽ እየሞከረ አልነበረም ይልቁንም ከእርሱ ጋር ለመጣበቅ እንጂ፡፡ "ካልባረከኝ አልቀህም"  ብሎ አለቀሰ፡፡ ይህ አመፀኝነት ሳይሆን ከእግዚያብሔር ጋር ያለ ግንኙነት ነው፡፡ 


ከእግዚያብሔር ጋር መታገል ማለት ነገሮችን ባልተረዳችሁባቸው ሁኔታ እንኳን ከእርሱ ጋር ለመሆን ልባችሁ ግን ክፍት ነው፡፡የእናንተ እቅድ እየገፋችሁ ሳይሆን ይበልጡንም ወደ እግዚያብሔር ሲያቀርባችሁ ማለት ነው፡፡እንደ ያእቆብ እያነከሳችሁ ልትሄዱ ትችላላችሁ፡፡ያ ማለት ህያው እግዚያብሔርን እንዳገኛችሁት ያስታውሳችኋል፡፡ያ ለሊት የያእቆብን  ማንነት ለዘላለም ቀይሮታል፡፡ ከእንቢተኝነት ወቶ ወደ እስራኤል ሄደ፣ ማለትም ከእግዚያብሔር ጋር ታግሎ አሸናፈ፡፡

 

እኔም በትግሎቼ ውስጥ የተማርኩት ይሄንን ነው፡፡ ቃላቶች እስኪያጥሩኝ የፀለይኩባቸውና ያነባሁባቸው ለሊቶች ነበሩ፡፡ በእግዚያብሔር ፈቃድ እና በእኔ ፍላጎት የመገፋፋት ሁኔታ ውስጥ ግን መንፈስ ቅዱስ እንዳልተሸፈንኩ ያሳየኝ ነበር፡፡ እየሰተሰራሁ ነበር፡፡ እምቢተኝነቴ ወደ እጅ መስጠት ተቀየረ፡፡ጥያቄዎቼ ወደ መስማማት፣ፍልሚያዬ ወደ እምነት ተቀየሩ፡፡


መታገል የተቀደሰ ነው፤ ምክንያቱም አሁንም በእግዚያብሔር እጆች ላይ ናችሁ ማለት ነው፡፡ነገሮች ባይገቡንም እንኳን፣ ከመሸሽ ይልቅ የእርሱን እጅ መያዝ እየመረጥን ነው፡፡



የጸጋ ሀሳብ

-ከእግዚያብሔር ጋር መጣላት በኩራት ላይ የተተከለ ነው፡፡

-ከእግዚያብሔር ጋር መታገል  በመፈለግ ላይ የተተከለ ነው፡፡

-አንዱ የእርሱን እጅ ሲገፋ

-ሎላኛው ደግሞ የእርሱን እጅ ይይዛል፡፡

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page