top of page
Untitled design (5).jpg

መልእክት ለቤተክርስቲያን

  • Writer: Naomie Deborah Tilahun
    Naomie Deborah Tilahun
  • Jun 24
  • 1 min read




መልእክት ለቤተክርስቲያን

በ ናሄሜ ዲቦራ ጥላሁን

ለተወደዳችሁ የቤተክርስቲያን ቤተሰቦች


የህን መልእክት የምጽፍላችሁ ጥቂት ሰዎች እነደማይረዱት ሁሉ፣ ክርስቶስን እንደተወ ሰው ሳይሆን በወጀብ መሀል ከክርስቶስ ጋር እንደተጣበቀ ሆኜ ነው፡፡በዚህ ወጀብ ውስጥ ሆኔ አንኳ የአይምሮ ህመምተኛ የመባልን ከባድ ጫና ተሸክሜው እገኛለሁ፡፡አለም በዚህ መልኩ ብትፈርጀኝም  እንኳ የእግዚአብሄርን ጣቶች ግን አለቀኳቸሁም፡፡ምክንያቱም የኔ ትክክለኛ ማንነት በሱ በክርስቶስ ብቻ የሚገለጽ መኆኑን አውቃለሁ፡፡


የመዝሙረኛው ዳዊት (44፣20-21) ቃላቶች የልቤን ጩኸት ያስተጋባሉ፡-

የአምካችንን ስም ረስተን ቢሆን እጃችንንም ወደ ሌላ አምላክ አንስተን ቢሆን እግዚአብሔር ይህንን አይመረምርም ነበርን?እርሱ ልብ የሰወረውን ያውቃልና፡፡


ይህ ቃል የኔ እውነታ ነው ደግሞም እግዚአብሔር የልቤን ያውቀዋል፡፡እርሱ ፊቴን በፍጹም ወደ ሌሎች አማልክት እንደማላማትር በእርግጥ ያውቀዋል፡፡በጨለማና ግራ በመጋባት ግዜያቶቼ ውስጥ ሁሉ ሌሎች በእግዚእሄር ላይ ያለኝን እምነት ቢጠራጠሩም እንኳን  እኔ ግን መሸሸጊያዬ ከሆነው ወደ አምልኬ መጸለይን አላቆምኩም፡፡የምናገረውን ሌሎች በቅጡ ባይረዱኝም ሌቤ ግን ወደ እሱ መቃተትን አላቆመም፡፡


በሁለንተናዬ ለክርስቶስ ያለኝን ፍቅር እንድትረዱኝ እሻለሁ፡፡ያጋጠሙኝ ተግዳሮቶች ከጌታ እየሱስ ጥላ ስር እንድርቅ አላደረገኝም፡፡ እዲያውም ይበልጡኑ ወደ እሱ እንድቀርብ አድርጎኛል፡፡በሌሎች ሰዎች የሚሰጠኝ ማንነትና መገለጫ ለኔ የሰማይ ፍርድ ሊሆኑ አይችሉም፡፡እኔ በእግዚአብሄር ዘንድ የተወደድኩ፣የተመረጥኩና ልጄ ብሎ የሚየራኝ ስለሆንኩ፡፡እኔም ከእርሱ ዘንድ አልራኩም እሱም በፍጹም ብቻዬን አልተወኝም፡፡


ወንድሞቼና እህቶቼ፣በማግለል መነጽር ሳይሆን በክርቶስ ጸጋ እንድተመለከቱኝ በጌታ ፍቅር እጠይቃችኋለሁ፡፡ማንኛውም ህመም፣የሰዎች ስም መስጠትና በተሳሳተ መንገድ መረዳት ከእግዚብሔር ፍቅርና ከእየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ሊለየንና ሊያርቀን እንደማይችል እኔ ህያው ምስክር ነኝ፡፡


በዚህ አለም ስንኖር እያንዳንዳችን የራሳችን ውጊያ ቢኖርብንም በርህራሄ መንፈስ አንደ አንድ አካል ሆነን እጅ ለእጅ ተያየዘን እንድንቆም ይሁን፡፡የልብን ሚስጥር ከሚያውቀው፣እሱን ዘወትር እንደምንሻ


ከሚረዳን ከእግዚአብሄር አይናችንን ላፍታም እንዳንነቅል ይሁን፡፡

ከፍቅርና ከጸና እምነት ጋር

Recent Posts

See All
A Letter to the Church

Beloved Church Family, I write to you not as one who has abandoned the Lord, but as one who has clung to Him through storms that few could understand. My journey has included the painful weight of bei

 
 
 

Comments


bottom of page